ከመሰሎቹ ጋ ስንቁን ሸክፎ ቶሎ በል እያለ
የልቡ ላይ እሳት ስሜቱን ቢያንረው እየገነፈለ
ሀገር ማለት ካሳብ የገዘፈች ትልቅ ምታስጠልል ዋርካ ጥላ
ሀገር ማለት ስትኖር ምታኖር ስጠፋ ምንጠፋ ታላቅ ሚስጥር
ሀገር ማለት የትም አለም ስንዞር በልባችንም ውስጥ የምንሸከማት
ሀገር ማለት ከወዛችን ላይ አለች ከገፃችን አለች እኛ ላይ ተስላ
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ኢትዮጵያ የተባለችው ሀገር
እንግዲህ የእናት ፍቅር የዘውድ ክብር የሚስት የዋህነት
የልጅ ደስታ የመቃብር ከባቢነት እንዲህ መሆኑን እወቅ
ካድማሱ ወዲያ ተሻግሮ ሄዶ ሰው ሀገር ላይ
ሀብት ስልጣኔ ልቡን የሚያሸፍት አይቷል ሲሳይ
የሰማይ የምድር እርቀቱን አይቶ እንዴት ሆነ እያለ
ማነው የጎተተኝ በሚለው ጥያቄ ተብሰለሰለ
ሀገር ማለት በብዙ ሰው ሀሳብ ውስጥ ምትመላለስ ምታብሰለስል
ሀገር ማለት ሲዳብሷት ምትሞቅ መአዛዋ ሚሸት ድንቅ ፍጥረት
ሀገር ማለት ምድራዊ ፍጥረቷ ከዘመን ተሳስሮ ትዝታን የሚያጭር
ሀገር ማለት ቢርቋት የምትቀርብ ሲቀርቧት ምታቅፍ እናት ነገር
አ..... ኢትዮጵያ ሀገሬ መመኪያዬ ክብሬ
አ..... ኢትዮጵያ ሀገሬ ዞሮ መግቢያዬ በሬ
አ..... ኢትዮጵያ ሀገራችን መመኪያ ክብራችን
አ..... ኢትዮጵያ ሀገራችን ዞሮ መግቢያ ቤታችን
አ..... ኢትዮጵያ ሀገራችን ዞሮ መግቢያ ቤታችን